እኛ ለኛ በስደት የተቋቋመው ሊባኖስ ሀገር ውስጥ ባሉ የቤት ሰራተኞች ነው። ተቋማችን የሚንቀሳቅሰው ማሕበረሰቡን ባማከሉ የሴቶች መብት ተሟጋች በሆኑ አክቲቪስቶች ሲሆን ትኩረት የሚያደርገው በድህነት ውስጥ ካሉ ሀገራት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተሰደው በቤት ውስጥ በሚሰሩ ሴቶች ጉዳይ ላይ ነው። በተለይም ሊባኖስ እና ኢትዮዽያ ሀገራት ባሉ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። በስደት ላይ ያሉ የቤት ሰራተኞች በየእለቱ ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች ሁለንተናዊ መፍትሔ እንሰጣለን። የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ሕጋዊ፣ የመኖርያ ቤት እና የምግብ ድጋፍ፤ እንዲሁም የመጠለያ ድጋፍ አና የህክምና አገልግሎት ሪፈራል ወይም ምልከታ መስጠት፤ የሙያ ስልጠና መስጠት እና ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እና ወደ ማሕበረሰቡ ለመቀላቀል የሚያስችሉ ድጋፎችን ማድረግ ነው።
እኩልነት፣ ብቃት/ብርታት (ኢምፓወርመንት)እና ፍትሕ በቀድሞ እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ በሊባኖስ እና በለሎች የመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት ላይ በስደት ላሉ የቤት ሰራተኞች። እገዛ የሚፈልጉ በስደት ያሉ የቤት ሰራተኞችን በመደገፍ እንዲሁም በማሕበረሰቦቻችን ውስጥ ያሉ ታዳጊ እና አዋቂ ሴቶችን በማበረታታት እና በማብቃት የካፋላ ስርዓትን ለማስወገድ የሚያስችሉ ማሕበረሰባዊ እንቅስቃሴ የመፍጠር አስተዋጽዖ እናደርጋለን። ይህንንም የምናደርገው ግንዛቤ በማስጨበጥ እና ሴቶችን በመደገፍ እንዲሁም መብታቸውን እንዲገነዘቡና እና እንዲያውቁ በማድረግ ነው።
ልዩነቶችን የሚቀበል፣መድሎዎ፣ በደል እና ብዝበዛ የሌለበት፤ እንዲሁም በስደት ያሉ የቤት ሰራተኞች መብትና በራስ የማድረግ እና የመወሰን አቅም መሉ በሙሉ የሚከበርበት እና የሚበረታታበት ማሕበረሰብ ማየት።
ሁሉም በስደት በሊባኖስ ውስጥ ያሉ የቤት ሰራተኞች እንዲሁም ከመካከለኛው ምስራቅ ከስደት ተመልሰው በኢትዮዽያ የሚኖሩ ሴቶች።
Labor - forced confinement - health - liberty and security of person (rape-forced abortion) - - access to justice freedom of movement (trafficking).
Kafala system that privileges the sponsor - lack of accountability, justice and protection for MDW vs. sponsors, agencies, insurance agencies (profiteers) - guilty until proven innocent; no due process - exclusion from labor law. More populous, underage girls, language barriers, low education => added discrimination
ሊባኖስ፥: Abolish kafala - fair, protective system free of impunity - laws to protect MDW.
ኢትዮዽያ፥: Child trafficking stopped - awareness/ transparency, enforcement of laws targeting human traffickers and abusers.
ሊባኖስ፥ ራስን ማጥፋት፣ የነፍስ ግድያ እና የአካል/የስነ-ልቦና ጉዳቶችን ይከላከላል። ፍትሕ የማግኘት መብት ይረጋገጣል፤ ከአደጋ እና በደል ነፃ የሆነ የስራ አካባቢ እና ሁኔታ በስደት ላሉ የቤት ሰራተኞች ይፈጠራል፤ ኤጀንሲና ስፖንሰሮች በስደት በሊባኖስ ባሉ የቤት ሰራተኞች ላይ ያላቸው ሙሉ በሙሉ የሆነ የበላይነት እና ተቆጣጣሪነት ይቆማል፤ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት ይረጋገጣል፤ በስደት ያሉ የቤት ሰራተኞች ድምፅ ይኖራቸዋል፤ በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ስደተኛ የቤት ሰራተኞችን ከፆታዊ ትንኮሳ እና ጥቃት እንዲሁም በዘረኝነት ላይ ከተመሰረቱ ጥቃቶች እና መገለል ከለላ ያገኛሉ።
ኢትዮጵያ፥ በኢኮኖሚ ራስን መቻል፤ በኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ተመልሰው ያሉትን በገንዘብ አያያዝ እና አጠቃቀም ዙሪያ ብቃት፤ በወንድ የቤተሰብ አባላት ከሚደርስ መድልዎ እና የገቢ መነጠቅ ጥበቃ
ሊባኖስ፥ የአሰሪ እና ሰራተኛ ግንኙነት፤ በግል ህይወት ውስጥ ጣልቃ አለመግባት እና ከስራ ጋር ያልተያያዙ የሰራተኛ የህይወት ክፍሎች ላይ ቁጥጥር ማቆም፤ ሰብዓዊነት እንደሌለው እንደ እቃ ሰዎችን ማየት ማቆም፤ ደሞዝ፣ የጤና አገልግሎት እና በነፃነት የመንቀሳቀስ መብቶች ይረጋገጣሉ።
ኢትዮዽያ፥መድሎን መቀነስ፣ የበለጠ ርሕራሔ ማሳያት፣ በስደት ያሉ ወይም የነበሩ የቤት ሰራተኞችን እንደ ገንዘብ ምንጭ ብቻ ማየት ማቆም፣ ለሰራተኞች ህጋዊ ጥበቃ ማድረግ
የአጠቃላይ የማህበረሰቡ የአስተሳሰብ እና የባሕሪ ለውጥ፣ የሰራተኛ እና አሰሪ ህጎች መከበር፣ ፍትሐዊ ያልሆነውን ስርዓት ከለላ አድርጎ ብዝበዛ አለማረደግ
Labor - health - liberty and security of person (rape-forced abortion) - freedom of movement (trafficking) - access to justice - self-determination/ agency.